Hands to the Plow logo

ቋንቋ

gears

የመጽሐፍ ቅዱስ ነገረ መለኮት ጠቃሚ ትምህርቶች

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ መለኮት መጽሐፍ ቅዱስ በክርስቶስ ውስጥ እንዴት እንደሚዳብር፣ እንደሚዋሃድ እና እንደሚጠቃልል ያብራራል። ከዚህ በታች ያሉት ጠቃሚ ትምሕርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን ቃላት ከመረዳት እና ከመተግበር ጋር የተያያዙ ናቸው። እነዚህም ጠቃሚ ትምህርቶች በሦስት ምድቦች ተከፍለዋል።

old-testament

የብሉይ ኪዳን ትምህርቶች

ጥንታውያን አይሁዶች በብሉይ ኪዳን የሚገኙትን መጻሕፍት በሦስት ክፍሎች ማለትም ሕግ፣ ነቢያትና ጽሑፎች በማለት ከፋፍሏቸው ነበር። ስለዚህ በዚህ ሥርዓተ ትምህርትም ውስጥ ይህን ጥንታዊ አደረጃጀት ተከትለናል።

ሕጉ

በሕጉ ውስጥ አምስት መጻሕፍት አሉ፤ እነዚህም፡- ዘፍጥረት፣ ዘጸአት፣ ዘሌዋውያን፣ ዘኍልቍ እና ዘዳግም ናቸው።

ነቢያት

በነቢያት ውስጥ ስምንት መጻሕፍት አሉ፤ እነዚህም፡- ኢያሱ፣ መሳፍንት፣ 1–2 ሳሙኤል (ይህ እንደ አንድ መጽሐፍ ይቆጠር ነበር)፣ 1–2 ነገሥት (ይህም እንደ አንድ መጽሐፍ ይቆጠር ነበር)፣ ኤርምያስ፣ ሕዝቅኤል፣ ኢሳይያስ እና አሥራ ሁለቱ (አሥራ ሁለቱ “ታናናሾቹ ነቢያት” እነዚህም እንደ አንድ መጽሐፍ “አሥራ ሁለቱ” ተብለው ይጠራ ነበር)።

ጽሑፎች

There are eleven books in the Writings: Ruth, Psalm, Job, Proverbs, Ecclesiastes, Song of Songs, Lamentations, Daniel, Esther, Ezra-Nehemiah, and 1–2 Chronicles. (Ezra and Nehemiah were considered one book. Chronicles was considered one book.)

new-testament

የአዲስ ኪዳን ትምህርቶች

አዲስ ኪዳን ሀያ ሰባት መጻሕፍትን ያካትታል። እነዚህ መጻሕፍት በተለያየ መንገድ ሊደራጁ ይችላሉ። በዚህ ሥርዓተ ትምህርት፤ እነዚህን መጻሕፍት በሦስት የተለያዩ ክፍሎች ተከፍለዋል፡- ወንጌላትና የሐዋርያት ሥራ (ሁሉም የታሪክ መጻሕፍት ናቸው)፣ መልዕክቶች እና ራዕይ። እያንዳንዱ ክፍል የተለያዩ የሥነ-ጽሑፍ ዓይነቶችን ያቀርባል፤ በመሆኑም እያንዳንዱ ክፍል የተለየ ተግባር ያከናውናል ማለት ነው።

ወንጌላትና የሐዋሪያት ሥራ

የአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው ክፍል ማቴዎስን፣ ማርቆስን፣ ሉቃስን፣ ዮሐንስንና የሐዋርያት ሥራን ያጠቃልላል። እነዚህ አምስት መጻሕፍት ኢየሱስንና የቀደመችው ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ታሪካዊ ዳራ ይሰጣሉ። ከእነዚህ መጻሕፍት ውስጥ የመጀመሪያዎቹ አራቱ ብዙውን ጊዜ “ወንጌላት” በመባል ይታወቃሉ።

መልዕክቶች

በዚህ ክፍል ለሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የተጻፉ አሥራ ሰባት መልዕክቶች፤ እንደዚሁም ለግለሰቦች የተጻፉ አራት ደብዳቤዎች፤ በጠቅላላ ሀያ አንድ መለዕክቶች አሉ፡- ሮሜ፣ 1–2 ቆሮንቶስ፣ ገላትያ፣ ኤፌሶን፣ ፊልጵስዩስ፣ ቆላስይስ፣ 1–2 ተሰሎንቄ፣ 1–2 ጢሞቴዎስ፣ ቲቶ፣ ፊልሞና፣ ዕብራውያን፣ ያዕቆብ፣ 1–2 ጴጥሮስ፣ 1–3 ዮሐንስ እና ይሁዳ ናቸው።

ራዕይ

የአዲስ ኪዳን የመጨረሻ ክፍል አንድ መጽሐፍ አለው፡ እሱም የዮሐንስ ራዕይ ነው። ይህ መጽሐፍ የተፃፈው አብያተ ክርስቲያናት እና እያንዳንዱ ክርስቲያኖች ስደትን እንዲታገሡ እና ለክርስቶስ ታማኝ ሆነው እንዲቀጥሉ ለማበረታታት ነው።

gears

ርዕሶች

በዚህ ክፍል ውስጥ ያሉት ትምሕርቶች በአንድ የተወሰነ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ያተኮሩ አይደሉም። ከዚህ ይልቅ የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት በተወሰኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተግባራዊ የሚያደርጉ ናቸው።

እግዚአብሔር ለአፍሪካ ያልው ፍቅር ረጅም ታሪክ

(አፍሪካውያን ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል እየደረሰባቸውም ነው። ይህም አንድ ሰው እግዚአብሔር አፍሪካንና ነዋሪዎቿን በእውነት ይወዳቸዋል ወይ ብሎ እንዲጠራጠር ሊያደርገው ይችላል። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ዶ/ር ጄሰን ድሮሼ የእግዚአብሔርን ጥልቅ እና ዘላቂ ፍቅር ለአፍሪካ ለማሳየት ቅዱሳት መጻሕፍትን ይጠቀማሉ።)